Skip to main content
004

በሃገር አቀፍ ደረጃ ገቢራዊ እየተደረገ የሚገኘው አዲሱ የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ፖሊሲን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መጀመር የሚያስችል ስልጠና ለክልሉ ቴክኒክና ሞያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ እና ለክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እየተሰጠ ነው።

የካቲት 27/2018

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰጠው የሚገኘው የሚገኘው ይህ ስልጠና ለሪፎርም ተግባሪ የክልል ተቋማት አመራርና ባለሙያዎች በዱራሜ ከተማ ግብርና አዳራሽ እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው መልዕክት ያስተላለፉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የተቋማዊ ለውጥና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ አስቴር ይርዳው በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የአሰራር ስርዓትን ማዘመን አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን ተናግረዋል።

በፌዴራል ደረጃ በ4 ተቋማት ገቢራዊ እየተደረገ የሚገኘው ይህ የሪፎርም ተግባር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ6 የክልል ተቋማት የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች ገቢራዊ የሚደረግ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

ሀገራዊ የሪፎርም እሳቤን ውጤታማ ማድረግን ታሳቢ ያደረገው ይህ ስልጠና የባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራርን የሚጠይቅ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ወ/ሮ አስቴር ገልፀዋል።

ስልጠናው ተጨባጭ እቅድ የማዘጋጀት እና በቂ ተግባቦት የመፍጠር አካል ስለመሆኑም አስረድተዋል።

ሀላፊዋ አክለውም የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ውጤት የሚያመጣና ለተሻለ ለውጥ የሚያነሳሳ የድጋፍና ክትትል ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አዲሱ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ እና ፍኖተ-ካርታ

እንደ ሀገር መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ጠንካራ እና ዘመን ተሻጋሪ ተቋም ለመፍጠር ጉልህ አበርክቶ እንዳለውም ገልጸዋል።

በመድረኩ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ እና የፖሊሲዉ ፍኖተ ካርታ እንዲሁም የዝግጅት ምዕራፍ የሪፎርም ትግበራ ዕቅድ ቀርበዉ ዉይይት ተደርጓል፡፡