Skip to main content

የሰው ሀብት ልማትና ጥናት ዳይሬክቶሬት

የመንግስት ተቋማት የተሰጣቸውን ተልዕኮ እና ተልኮውን ለማሳካት የተነደፉ ራዕይ እና እሴቶችን እውን ለማድረግ አቅሙን የተገነባና ብቃት ያለው የሰው ሀይል እጅግ ወሳኝ ነው፡፡

የመንግስት ሰራተኛ መሆንና ዜጎችን ማገልገል የመንግስት ሰራተኞችን የሚያኮራ የክብር ምንጭ መሆኑን የሚገነዘቡና የተቋማቸውን ዓላማ እና ግብ ለማሳካት የሞራል ልዕልና ያላቸው የመንግስት ሰራተኞች ለማፍራት መግስትና ሌሎችም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል፡፡ በመልካም ስነ-ምግባር ታነጹ የመንግስት ሰራተኞች በማፍራት ፕሮፌሽናልና በውድድር የሚሰራ ሲቪል ሰርቪስ መገንባት የመንግስት የማስፈጸሚ አቅምን መገንቢያ ቁል ስራ ማድረግ ሌላኛው ተግባር መሆን አለበት፡፡ ብቃት ያለው የሰው ሀይል ሰምሪት ስርዓት ዝርጋታ የሚመለከቱ ጉዳዮች አሁን ካለው ሀገራዊና አለማቀፋዊ ሁኔታዎች አንጻር በመቃኘት ወቅቱን የሚመጥን የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት እውን ማድረግ አስፈላጊ የሆነበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ 

ብቃት ባላቸው የሰው ሀይል ያልተገባ ተቋም በህግ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በሚፈለገው ደረጃ ማሳካት አይታሰብም፡፡ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሚጠበቅበትን  ከፍተኛ ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት የሰው ሀይል አስታደርር ስምርት ብቃትን መሰረት ያደረገ መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ ወደ ስራ የተሰማራውና የሚሰማራው የመንግስት ሰራተኛ እራሱን ከወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ለማስኬድ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎች በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ  በዕቅድ በማስደገፍ ተግባራዊ በማድረግ የተቋማትን አፈጻጸም ማሳደግ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር በመሆኑ ሁለም የክልልና የታችኛው መዋቅር የመንግስት ተቋማት ከዚህ ተግባር አፈጻጸም አንጻር ራቻቸውን በመፈተሸ ፈጥነው ወደ ተግባር መግባት ያስፈልጋል፡፡

የሰለጠነ የሰው ሀይል በአይነትና በብዛት የማልማትና የማዘጋጀት ስራ ለሀገራዊ ልማትና እድገት ያለው ጠቀሜታ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ የሰው ሀይል ልማት ስራዎች በእቅድና በበጀት በተጨባጭ የማስፈጸሚያ ብቃት ላይ ካልተመሰረቱ የተቋማቱ የልማት ግቦች በሚፈለገው ደረጃ ማሳካት አይቻልም፡፡ እስካሁን እየተከናወኑ ያሉ የሰው ሀይል የማልማት ስራዎች ስትራቴጂካል አድረጎ ከመሄድ እና በክፍተት ጥናት ላይ የተመሰረተ ልየታ ከማድረግ አንጻር ሰፊ ጉድለት  ሚታይበት እና በዘፈቀደ የሚከናወን መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት የተሰበሰቡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ይህ ደግሞ የመንግስት ሰራተኛው በቂ የሆነ አቅም ፈጥሮ በመሄድ   በራስ መተማመን አዳብሮ ውጤታማ አገልግሎት ከመስጠት አንጻር የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽኖ አሳድሮበታል፡፡  ስለዚህ ሁለም ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመንና ከተደራሽነትና ከጥራት እንዲሁም ከወጪ አንጻር የህ/ተሰቡን /የተገልጋዩን/ ፍላጎት መሰረት ያደረገ እንዲሆን የሰው ሀብት ልማት ሰራው የተቋማት ቁልፍ እና ስትራቴጂክ ተግባር ተደርጎ ሊውሰድ የግድ ይላል፡፡ 

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቢሮ በሰው ሀብት ልማትና ስራ አመራር ዘርፍ ስር ከተደራጁ ዳይሬክቶሬቶች መካከል አንዱ  የሰው ኃብት ልማትና ጥናት ዳይሬክቶሬት ሲሆን ዳይሬክቶሬቱ ከሚያከናውናቸው ተገባራት መካከል ዋናዋናዎቹን ለጥቀስ ያህል ፣ 

በክልሉየሰው ሃብት ልማትን የሚመለከት ሥራን በማቀድ፣ በማደራጀትና በመምራት፣ ከሥራው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መመሪያዎች በማዘጋጀት፣ ጥናቶችን በማካሄድ፣ የአፈፃፀም ስልቶችን በመንደፍ፣ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ እና አፈፃፀሙን በመገምገም በተቋማት ብቃት ያለው የሰው ኃብት ማፍራት፣ የሰው ሀብት ብቃት ማረጋገጫ ስርዓት በመዘርጋት ፣ የክልሉ የመንግስት አገልግሎት በብቃት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን በማድረግ የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት  ማሳደግ፣ በክልሉ በአጭርና ረጅም ጊዜ የተሰጡ ስልጠናዎች በተቋማት አፈጻጸም ላይ ያላቸውን ፋይዳና በአፈጻጸም በሂደት ላይ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በሳይንሳዊ ጥናት በመለየት  ጥራት ያላቸው  ስልጠናዎች መስጠት የሚቻልበት ሁኔታ መፍጠር ፣ በክልሉ የመንግስት ሰራተኞች የውጭና የሀገር ውስጥ  ስልጠናዎች እንዲመቻቹ ሁኔታዎች ማመቻቸት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡ የነጻ የትምህርት እድሎችን ለተቋማት በፍትሀዊነት ተደራሽ ማድረግ እና ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ  ተግዳሮቶች ማረምና በአሰራር እንዲፈቱ ማድረግ ፣ እነዚህና ሌሎችም ዝርዝር ተገባራት ተካተዋል፡፡

ስለሆነም  ይህንን ተግባራት እውን ማድረግ የሚቻለው በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ ተቋማት የራሳቸው ድርሻ ሲወጡ በመሆኑ ተቋማት ከወትሮ በተለየ መልኩ የሰው ሀብት ልማት ስራው ትኩረት በመስጠት በህግ የተሰጣቸውን ተልኮ እውን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል