የሰው ሀብት አሰተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት
የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ የመንግሥት ሠራተኞችን አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ በመከተል የሚከተሉትን አብይ እና ቁልፍ ተግባራት ያከናውናል፡፡
- የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ተግባራት ያቅዳል፣ ያደረጃል፣ ይመራል፣ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል ይቆጣጠራል፣ የስራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ ክፍተቶችን ይለያል፣ ያበቃል፤
- የሰው ኃይል ልማት የሚመራ ገዢ ስትራቲጂና ዝርዝር ዐቅዶች እንዲዘጋጁና ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
- ከስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል ፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፤
- የሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ መመሪያዎች፣ የስራ ሂደቶች፣ ማዕቀፎችን እንዳግባቡ ተዋደው / ተቀርጸው ተግባራዊ እንዲሆኑ ይመራል ይቆጣጠራል፤
- በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በሰው ሀብት ሥራ አመራርና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት ይከታተላል፤
- በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት ከፍተኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የድስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፤
- አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፤
- ዘመናዊ የአፈጻጸም ምዘና ግምገማና ማሻሻል ስርዓት እንዲኖረው የሚያስችል የአፈጻጸም ምዘናና አመራር ስርዓት እንዲዘጋጅና ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤
- የሰው ኃይል ክህሎትና ብቃት ለማሳደግ የሚያስችል የሰው ኃይል ልማት ፡ ስልጠናና ትምህርት ዕቅድና መርሃ ግብር እንዲዘጋጅና እንዲተገበር ያደርጋል፤
- የአመራር ብቃትና ዝግጅት ለማሳደግ የሚያስችል የተከታይ ማፍራትና የሞያ ዕድገት ስትራቴጂ፣ ዕቅድና ስርዓት ዝግጅትና ትግበራ በበላይነት ይመራል ያስተባብራል ይቆጣጠራል፤
- የሰው ኃይል ልማት አገልግሎት አሰጣጥ ለማላቅ የሚያስችል የክዋኔ ትዕምርትና (operating model); የስራ ሂደት የቲክኖሎጂና የመረጃ ስርዓት ግንባታና ትግበራን
- አደረጃጀትና ተቋማዊ ዕድገት ብሎም ባህል በሚፈለገው አቅጣጫ ለማጎልበት የሚያስችል ቀጣይነት ያለው የተቋማዊ አቅም ግንባታ ማዕቀፍ፣ ስልትና ዕቅድ እንዲዘጋጅና ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤
- አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከፍተኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም የሰው ሀብት ሥራ አመራርን የተመለከቱ መመሪያዎች እንዲከለሱና አዳዲስ ጥናት እንዲጠኑ ያደርጋል፣ የጥናት ውጤቶችን ይገመግማል፤
- ከፍተኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም ለሥራ መደቦች የሥራ ትንተና ተከናውኖ የሥራ ዝርዝር መግለጫ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤
- ከፍተኛ አደረጃጀት ያለው ተቋም ሠራተኞች መንግሥት ባወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ በምዘናው ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን እንዲከናወኑ ያደርጋል፤