Skip to main content

የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ድጋፍና ክትትል ዘርፍ

1. የዘርፉ ተልኮ

በክልሉ የመንግስትን ፖሊሲዎችና ስትራቴዎች በብቃት ለመፈጸም የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮችንና አደረጃጀቶችን በመዘርጋት፣ተቋማዊ የመልካም አስተዳደር ግንባታ ስራን ለማጠናከር የመልካም አስተዳደር መርሆዎች በአግባቡ እንዲተገበሩ ለማድረግ  የአመራሩንና  መንግስት ሠራተኛዉን  በመለወጥና  ብቃቱን በማሳደግ፣ህዝብን በቅንነትና በታማኝነት የሚያገለግል ጠንካራና ዉጤታማ ሲቪልሰርቪስ በመፍጠር ጠንካራ የመንግሥትአገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን መገንባት ፡፡

2. መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥ የአመለካከትና የዕይታ ለዉጥ ማድረግ፤

መንግሥታዊ አስተዳደር ማለት መንግስት የሚያወጣቸውን ፖሊሲዎች እና ኘሮግራሞች በውጤታማነት ተግባራዊ በማድረግ ህዝቡን የሚያገለግልበት፤ እንዲሁም መንግስታዊ አደረጃጀቶችና አሰራሮች፣ ህጐች፣ መመሪያዎች እና ውሳኔዎች የሚተላለፉበትና ተግባራዊ የሚደረጉበት ስርዓት ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንደለ መንግስታዊ አስተዳደር መልካም ወይም መልካም ያልሆነ ሊሆን ይችላል፡፡ 

መልካም አስተዳደር ወጥ የሆነና ሁሉም ሰው የሚስማማበት ትርጉም ባይኖረውም የመልካም ነገሮች ሁሉ ድምር ውጤትና መልካም ያልሆኑና ኢ-ፍትሐዊ ነገሮችን ሁሉ የማስወገድ ሂደት ነው፡፡ በአንድ ሀገር መልካም አስተዳደር እየሰፈነ ሲሄድ የልማት ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እና በመንግስት ተቋማት በሚሰጡ በመንግስታዊ አገልግሎቶች የዜጎች እርካታ እየተረጋገጠ ስሄድ  መልካም የሆነ አስተዳደር ዕዉን በመሆኑ የሀገር ህልዉና ቀጣይነት ጭምር ይረጋገጠል ማለት ነው፡፡

እንደ ክልል በሁሉም ደረጃ በሚገኙ የመንግስት አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት እንዲቻል ስምንቱንም የመልካም አስተዳደር መርሆዎች ማለትም፡- አሳታፊነት /participation/፣ የጋራመግባባት / Mutual understanding/፣ፈጣን ምላሽ መስጠት /Responsiveness/፣ ግልፀኝነት /Transparency/ ፣ተጠያቂነት /Accountability/፣ ፍትሃዊነትና አካታችነት (equitable and inclusiveness)፣ የህግ የበላይነት / Rule of law/፣ ቅልጥፍናና ውጤታማነት /Efficiency and Effectiveness/ የሚሉ የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን በአግበቡ ከለመተግበር ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እንደ ክልል የመንግስት አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት አካባቢ በመርሆዎቹ አተገባበር ዙሪያ የሚተየዉን የወጥነት ጉድለት ፈጥኖ ማረም ይገበል፡፡ 

ሌለዉ የመልካም አሰተዳደር ችግሮችን በተለይም ተቋማት ለተገልጋዮቻቸው ከሚሰጡት ከመንግስታዊ አገልግሎት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በአግባቡ ለመፍታት እንዲቻል ችግሮቹን የዉስጥ እና የዉጭ የመልካም አስተዳደር ችግር በሚል በአግባቡ ለይቶና የዕቅድ አካል አድርጎ በመያዝ እንዲሁም የመፍቻ ስልቶችንም ጭምር አስቀምጦ በመፍታት የተገልገዩን ህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማጠናከር በሂዳቱም የህዝብ እርከታ ለማረጋገጥ በትኩረት መስራትን ይጠይቃል፡፡ 

3. መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት በዘርፉ ትኩረት የሚሠሩ  ግብ ተኮር ተግባራት፥

    3.1.1 የመልካም አስተዳደር መርሆዎች ትግበራን ማጠናከር፣

    3.1.2 የዜጎች /የተገልጋዮች/ ቅሬታ ማስተናገጃ ሥርዓት ትግበራን ማጠናከር፤

    3.1.3 የህዝብ /የህዝብ ክንፍ/ ተሳትፎ ትግበራን ማጠናከር፤

    3.1.4 በመንግስት ተቋማት ውስጥ የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ትግልን ማጠናከር፤

   3.1.5 የገጠር ቀበሌ ነዋሪዎችን (አርሶ አደር) ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማሳደግ የሚሉ ግብ ተኮር ተግባራትን በትኩረት በመከናወን የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሠራ ይገኛል፡፡