አደረጃጀት፣ ስራ ምዘና እና ክፍያ ጥናት ዳይሬክቶሬት
ቢሮአችን አጠቃላይ ከሰው ሀብት ልማትና ሥራ አመራር አንጻር በክልላችን በየደረጃ ባሉ የመንግስት ተቋማት የሚከናወኑ ተግባራት የሚመሩበትን የአሰራር ሥርዓት መዘርጋትና ማስረጽ፣ በተቋማት ተግባራዊ እንዲሆኑ መከታተል፣ መደገፍ እና ክፍተቶችን መሰረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በመስጠት ሥራው ሊሳልጥ የሚችልበትን በጥናት ላይ የተመሰረተ የሰው ሀይል መዋቅር መፍቀድና ሥራዎችን በመመዘን ደረጃ መወሰንና የክፍያ ሥርዓቱን ማረጋገጥ ከሚያከናውናቸው ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ በዚሁ መሰረት ተገልጋዩ ህብረተሰብ በአገልግሎት አሰጣጡ እርካታ እንዲያገኝ በማድረግ ተቋማት በልማትና በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የሚኖራቸውን ተሣትፎ ማሳደግና የተሰጣቸውን ተቋማዊ ተልዕኮ በተገቢው መወጣት የሚችሉትን አቅም መፍጠር አንዱና ዋናው ግብ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በክልላች የመንግስት ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን የጠበቀ፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ለተገልጋዩ ተደራሽ ለማድረግ የሰው ሀብት ስራ አመራርና ልማት የአሰራር ስርዓቶችን በመፈተሽ መዘርጋትና የወጡ መመሪያና ደንቦችን ተግባራዊ በማድረግ ተገልጋዩ ህብረተሰብ በአገልግሎት አሰጣጡ እርካታ እንዲያገኝ ከማድረግ አንጻር ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛል፡፡ የአደረጃጀት ሥራ ምዘናና ክፍያ ጥናት ዳይሬክቶሬት ከዘርፉ የተሰጡትን አጠቃላይና ዝርዝር ሥራዎችን በዕቅዱ ውስጥ በማካተት በሩብ ዓመቱ ካቀዳቸው የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም በ3 ወራት የተከናወኑ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ከዚህ እንደሚከተለው ተዘጋጅቶ ቀርቧል።